Amharisk: ለሰፈሩ አዲስ ኖት?
በሪንግሳከር፣ ሐመር፣ ስታንግ እና ሎተን የከተማ መስተዳድሮች በሚኖሩበት ጊዜ ከቤት ውስጥ የሚወጣን ቆሻሻን የሚያስወግዱበት መንገድ ከዚህ በታች ተበራርቷል።
የእርስዎን ከቤት ውስጥ የሚወጣ ቆሻሻን በማስወገድ ወደ የሚተባበርዎት ሲርኩላ አይኬኤስ [Sirkula IKS] እንኳን በደህና መጡ።
እርስዎ የሚጥሉት ቆሻሻ አዳዲስ ነገሮችን ለመሥራት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ለዚህም ሲባል ነው እያንዳንዱን ዓይነት ቆሻሻ በመልክ በመልኩ በተቻለን መጠን ለይተን የምናስቀምጠው። ለምሳሌ፣ ጥቅም ላይ የዋሉ ወረቀት ነክ ነገሮች ወደ አዲስ የወረቀት ዕቃዎች፣ የጠርሙስ ጣሳዎች ወደ አዳዲስ ጣሳዎች እና የቆርቆሮ ጣሳዎች ወደ አዳዲስ ጣሳዎች ወይም ለምሳሌ ወደ ብስክሌትነት ሊለወጡ ይችላሉ።
በእኛ የምንጥለው ቆሻሻ ውስጥ ያሉትን መሠረታዊ ቁሳቁሶች ዳግም ጥቅም ላይ ማዋል ለእኛ ለራሳችን እና ለመጻኢ ትውልዶች ለሁለታችንም ከምድር የሚገኙ የተፈጥሮ ሃብቶችን ተገኝነት ብዛት መጨመር እንድንችል ያግዘናል።
በሪንግሳከር፣ ሐመር፣ ስታንግ እና ሎተን የከተማ መስተዳድሮች የሚገኙ ሁሉም መኖሪያ ቤቶች ተመሳሳይ የሆነ የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓትን የሚጠቀሙ ሲሆን ይህንንም ሲርኩላ [Sirkula] በበላይነት ይመራዋል። እያንዳንዱ መኖሪያ ቤት ለዚህ አገልግሎት ቆሻሻ ለሚሰበሰብበት ዓመታዊ የአገልግሎት ክፍያን ይከፍላል። በዚህ አገልግሎት ሥር የሚካተቱ አገልግሎቶች፦
የመኖሪያ ቤት ቆሻሻን መሰብሰብ
ከእርስዎ መኖሪያ ቤት አምስት ዓይነት የቤት ውስጥ ቆሻሻዎች ይሰበሳባሉ፦ የምግብ ትራፊ፣ ፕላስቲክ፣ ወረቀት፣ ምንም ዓይነት ጥቅም ላይ ሊውሉ የማይችሉ ቆሻሻዎች ጠርሙስ እና ብረት ነክ እሽጎች።
ለእነዚህ እያንዳንዳቸው የየራሳቸው የቆሻሻ መጣያ ዕቃ በግቢዎ ውስጥ ይኖርዎታል። እነዚህ ቆሻሻ መጣያ ዕቃዎች የሲርኩላ ንብረቶች ሲሆኑ አስፈላጊውን ክትትል ይኸው ድርጅት ያደርግላቸዋል፤ ዕቃዎቹ እርስዎ በሚኖሩበት ግቢ ውስጥ ሁልጊዜ መቀመጥ ይኖርባቸዋል። በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ፣ በአፓርታማ ብሎክ ወይም ተመሳሳይ ቤቶች የሚኖሩ ከሆነ የጋራ የሆኑ የቆሻሻ መጣያዎችን ከሌሎች ነዋሪዎች ጋር ሊጋሩ ይችሉ ይሆናል።
ደረጃቸውን የጠበቁ የቆሻሻ መጣያዎች እንደ የሚጣልባቸው ዓይነት ቆሻሻ የተለያየ ቀለም ያለው መክደኛ አላቸው። ከዚህ በተጨማሪ ለፕላስቲክ ቆሻሻ መሰብሰቢያ የሚሆን ለብቻው የተለየ ውስጡ ምን እንዳለ የሚያሳይ የፕላስቲክ ከረጢት ይኖርዎታል።
አራት ቆሻሻ መጣያ በርሜሎች እና አንድ ውስጡ የሚያሳይ የፕላስቲክ ቆሻሻን ለመሰብሰብ የሚያገለግል የፕላስቲክ ከረጢት እያንዳንዱ መኖሪያ ቤት በመደበኛነት የሚኖሩት የተመደቡለት የቆሻሻ መጣያዎች ናቸው።
የቆሻሻ መጣያ በርሜሉ እና ውስጡ የሚያሳየው የፕላስቲክ ከረጢት በተለያዩ እኩል ጊዜያት ልዩነት ይሰበሰባሉ፦
- የምግብ ትራፊ (ቡናማ መክደኛ) በየ 2 ሳምንቱ ይጸዳል።
- ፕላስቲክ (ውስጡ የሚያሳይ የፕላስቲክ ከረጢት)፣ ወረቀት (ሰማያዊ መክደኛ) እና ተመልሰው ምንም ጥቅም ላይ የማይውሉ ነገሮች (ግራጫ መክደኛ) በየ 4 ሳምንቱ ይጸዳሉ።
- ብርጭቆ እና የብረት እሽጎች የመሳሰሉ ቆሻሻዎች በየ 8 ሳምንቱ ይሰበሰባሉ።
ለበለጠ መረጃ Tømmekalender (የቆሻሻ አሰባሰብ ቀን መቁጠሪያ) የሚለውን ይመልከቱ - በየትኛው የሳምንቱ ቀን የቆሻሻ መጣያ በርሜሎቹ እንደሚጸዱ ለማወቅ www.sirkula.no - ን ይመልከቱ።
የቆሻሻ መጣያ በርሜሎች/የፕላስቲክ ከረጢቱ ቆሻሻው ከሚሰበሰብበት ቀን ቀደም ብሎ ባለው ምሽት ላይ ለመሰብሰብ እንዲመቹ ተደርገው ከቤት ውጭ ዝግጁ ሆነው መቀመጥ አለባቸው።
የምግብ ትራፊ ወደ በርሜሉ ከመቀመጡ በፊት ራሱ በራሱ በሚበሰብስ ልዩ ቡናማ ከረጢት ውስጥ ይቀመጣል። ወደ በርሜሉ ውስጥ ከማስቀመጥዎ በፊት ከረጢቱን በሚገባ እንዳይፈስ አድርገው እንደቋጠሩት ያረጋግጡ።
ለምግብ ወይም ለፕላስቲክ ቆሻሻ እንዴት አዲስ ከረጢቶችን ማግኘት እንደሚቻል
ለፕላስቲክ ቆሻሻ ጥቅም ላይ የሚውለው ውስጡ የሚያሳየውን የፕላስቲክ ከረጢት ሲያልቅብዎት ምንም ነገር የሌለበት ባዶ ዝርግ የፕላስቲክ ከረጢት (ከሱፐር ማርኬት የሚሰጠው ከረጢትን ወይም ሌላ ዓይነት የፕላስቲክ ከረጢት) ቆሻሻ ከመሰብሰቡ በፊት በቆሻሻ በርሜሉ ላይ በመቋጠር አዲስ የከረጢት ጥቅልን ማግኘት ይችላሉ። የእርስዎ ቆሻሻ በሚወሰድበት ጊዜ በዚህ መልኩ አዲስ የከረጢቶች ጥቅል ይሰጥዎታል። አዲስ የፕላስቲክ ከረጢቶች ጥቅል ልክ እንዳገኙ ከቆሻሻ መጣያ በርሜሉ ላይ የቋጠሩትን ባዶ የፕላስቲክ ከረጢት ማስወገድ እንዳለብዎት አይዘንጉ።
ቡናማው የምግብ ትራፊ ማጠራቀሚያ የቆሻሻ ከረጢት ሲያልቅብዎት ቆሻሻ ከሚሰበሰብበት ቀን ቀደም ብሎ ቡናማ የምግብ ትራፊ ከረጢትን በቆሻሻ መጣያ በርሜሉ ላይ በመቋጠር አዲስ ከረጢቶችን ማግኘት ይችላሉ። የእርስዎ ቆሻሻ በሚወሰድበት ጊዜ በዚህ መልኩ አዲስ የከረጢቶች ጥቅል ይሰጥዎታል።
ከዚህ በተጨማሪ አዳዲስ የፕላስቲክ ቆሻሻ መጣያ ከረጢቶችን እና የምግብ ትራፊ መሰብሰቢያ ከረጢቶችን በዳግም አድሶ መጠቀሚያ ጣቢያዎች፣ ከማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።
ቆሻሻን ወደ መልሶ ማደሻ ማእከላት ራስ ወስዶ ማድረስ
ከምግብ ትራፊ በስተቀር ሁሉንም ዓይነት ቆሻሻ በሥራ ሰዓታት በሰው ወደ የሚንቀሳቀሱት የመልሶ ማደሻ ማእከላት ራስዎ ወስደው ማድረግ ይችላሉ። በተለይ ለሕዝብ ጤና እና ለከባቢያዊ አየር አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ነገሮችን አደጋ ከማድረሳቸው በፊት መከላከል እንዲቻል መርዛማነት ያላቸውን ቆሻሻ ቁሳቁሶች ወደ ዳግም ማደሻ ማእከላት ራስዎ አምጥተው ማስረከብዎ እጅግ አስፈላጊ ነው። መርዛማ ቆሻሻ ሲባል እንደ ባትሪዎች፣ የመብራት አምፖሎች፣ ቀለም፣ የጋዝ ቆርቆሮዎች፣ ዘይት፣ ጸረ-ተባይ መርዞች እና የአረም ማጥፊያዎች፣ የሞባይል ስልኮች፣ የኤሌክትሪክ ሽቦ ገመዶች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ሌሎች ኤሌክትሪክ የሚጠቀሙ ምርቶችን ማለታችን ነው።
መርዛማ ቆሻሻ ለመጣል፡ ቀዩን ፌስታል ይጠቀሙ።
ከምግብ ትራፊ በቀር ወደ ዳግም ማደሻ ማእከላት የግል የሆነን የቤት ቆሻሻን ወስዶ በማስረከብ ምክንያት የሚከፈል ምንም ዓይነት ተጨማሪ ክፍያ የለም። sirkula.no ገብተህ ክፍያውን መመልከት ይችላሉ።
በዳግም አድሶ መጠቀሚያ ጣቢያዎች፣ ተመልሰው ምንም ጥቅም ላይ የማይውሉ ነገሮች ለመጣል ውስጡ የሚያሳይ የፕላስቲክ ከረጢት ይጠቀሙ። እነዚህ የፕላስቲክ ከረጢቶች፡ ከሱፐር ማርኬት ወይ ከሲርኩላ መግዛት ይችላሉ።
የዳግም ማደሻ ማእከላት የጎዳና አድራሻ፦
- Kretsløpsparken gjenvinningsstasjon, Arnkvernvegen 169, Hamar
- Brumunddal gjenvinningsstasjon, Jemtlandsvegen 11, Brumunddal
- Moelv gjenvinningsstasjon, Industrivegen 14, Moelv
- Stange gjenvinningsstasjon, Hansrudvegen 1, Stange
- Heggvin gjenvinningsstasjon og avfallsanlegg, Arnsetvegen 41, Vang på Hedmarken
- Sirkula administrasjon, Arnkvernvegen 169, Hamar
በሚከተለው አድራሻ ላይ የዳግም ማደሻ ማእከላቱን የሥራ ሰዓታት ማግኘት ይችላሉ፦ www.sirkula.no
የእርስዎን የቤት ቆሻሻ በመልክ በመልኩ ስላስቀመጡ እናመሰግናለን!
ቆሻሻንበመልክበመልኩማስቀመጥንበተመለከተእገዛማግኘትከፈለጉ፦ www.sirkula.noይጎብኙ
ለ የሚያገለግልዎት ቆሻሻን በመልክ በመልኩ የመለያ ዘዴ መመሪያ ከዚህ በታች ተሰጥቷል
ቆሻሻ የሚሰበሰብባቸውን ቀናት መተግበሪያውን በእርስዎ ስልክ ላይ በማውረድ (ዳውንሎድ በማድረግ) አስቀድመው ማስታወሻ የጽሑፍ መልእክት በስልክዎ ላይ ያግኙ፦ Min Renovasjon (IOS - Android)
Sirkula IKS
አድራሻ፦ P.O Box 3, 2301 Hamar
ስልክ ቁጥር፦ 62 54 37 00
ኢሜይል፦ Post@sirkula.no
ድረ-ገጽ፦ www.sirkula.no